አዲስ ዘመን ሀሙስ ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም
የተተው ዕቃዎች ግልፅ ጨረታ ቁጥር 7-62/2017 ጨረታ
በኢትዮጵያ
ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 160/201 መሰረት የተተው ወይም
የተወረሱ ዕቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሠረት የተተው ንብረቶችን ማለትም TYRE WITH
FLAP AND TUBE፣ PVC SHATTAF SIZAE: LED STRINGLIGHTSAND USB POWERED
WATERPROOFFAIRY LIGHTS: ALUMINUMALLOY TOWER RULER ANGLE VALVE ENGINE CERIA
GUASKET: BIODIGESTERSISREMA 12COMPLETE WITH FITTINGS: DISEL GENERATOR SET WITH ATS፣
VACUUM COOLING MACHINE AND GLACIAL ACETIC ACID እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚህም
መሠረት ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች
በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. ተጫራቾች
የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ መግለጫ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ
ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡oo ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ
5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡oo እስከ ቀኑ 5፡30 የማይመለስ ብር
100 (አንድ መቶ) በመክፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳቦች ቡድን መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች
በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት
እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር
500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ፡፡
3. ማንኛውም
ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ
ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMSSON
MOD]O BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት።
ተሳታፊዎች ዋጋ መሙላት የሚችሉት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተዘጋጅቶ ማህተም ያረፈበት ሠነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች
የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አሰቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን
አይወስድም፡፡ በጨረታ ተሸጦ የተወሰደ ዕቃ ተመላሽ አይደረግም፣ ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም።
5. የግልፅ
ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃዎች ለመግዛት የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ፤ የሞሉበት ሠነድ፤ በተራ ቁጥር 2 የተገለፁትን
ማስረጃዎች ኮፒ እና ያቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO በኤንቬሎፕ ወይም በፖስታ
በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት እስከ የመጨረሻው ቀን ጠዋት 4፡45 ድረስ በቅርንጫፍ
ጽ/ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል። የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
6. የጨረታ
ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ የወጣበት ቀንን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ጠዋቱ 5፡00 ላይ ተጫራቾቹ
ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
7. ማንኛውም
በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ
አይችልም፣ በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታው
ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም እና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ
የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
8. የግልጽ
ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ
ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ
CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
9. በተራ
ቁጥር 8 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ
የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።
10. አሸናፊው
ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።
11. ቅርንጫፍ
ጽ/ቤቱ ለጨረታ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው። በጨረታ ተሽጦ በጨረታ አሸናፊው የተወሰደ እቃ
አይመለስም፡፡
12. ቅርንጫፍ
ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ለተጨማሪ
ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 022-236-90-94 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት