አዲስ ዘመን ቅዳሜ ግንቦት 10 ቀን 2016ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር PPS/VP-6FBl/08/09/2016
የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ እንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ደን ልማት፣
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የማዕድን ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት
ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው
1, በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ
ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. 6 ኪሎ በሚገኘው የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ህንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 007 በመምጣት የተሽከርካሪዎቹን
ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000.00 ብር በመንግሥት ግዥ አገልግሎት
የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785oi8 ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ
10፡oo ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
4. ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ እና የጉምሩክ ቀረጥ ግብር ወጪ ካለው ባለንብረቱ መሥሪያ
ቤቱ የሚሸፍን ሲሆን የስም ማዛወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው ይሸፈናሉ፣
5. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሽከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ
በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ
የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል፡፡ የተሽከርካሪውን የመነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች
ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ
ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
7 የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:00 መወዳደር ይችላሉ።
ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ
ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ
ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፤
8 በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ 7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ
የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት
የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል::
9 በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ተሽከርካሪዎች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ
ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
10. አገልግሎቱ ያወጣውን ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
11.አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሽከርካሪውን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት
ግዴታ አለባቸው፣
12 አገልግሎቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ
የተጠበቀ ነው፣
13 ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-154-04-25 ወይም 011-122 37- 08/36
ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
የመንግሥት ግዥ አገልግሎት
አዲስ አበባ