አዲስ ዘመን ማክሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2017ዓ.ም
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጣበስፋ/ ብግሽጨ /12/2017
የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የተለያዩ ዕቃዎችን ማለትም፡-
በሎት -1 ዩፒቪሲ ፓይፖች
በሎት-2 የተለያዩ የማለስለሻ ዘይቶች እና
በሎት-3 3294 ኩንታል ያልተፈለፈለ ሩዝ በግልጽ ጨረታ አወዳደድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን
ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ/
የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤
በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት
አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
3. ጨረታው ሚያዝያ 08 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ
ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በቁጥር 4 ላይ በተገለፀው አድራሻ
ሚያዝያ 08 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 300.00 /ሶሰት መቶ ብር/ ብቻ በጣና በለስ
ስኳር ፋብሪካ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000057735167 ገቢ በማድረግ ከታች በተመለከተው አድራሻ ዘወትር በስራ
ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ከምሳ በኋላ ከ7፡00-1፡00 ሰዓት ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00
መግዛት ይችላሉ፡፡
5. የጨረታው ማስረከቢያና መክፈቻ አድራሻ
አዲስ አበባ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተዘንስ ሆስፒታል አካባቢ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንጻ፡፡
ብሎክ A ቢሮ ቁጥር B008
ስልክ ቁጥር 011 5‐586725/0912031748
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ፐርሰንት |ሁለት ከመቶ/ በባንክ
የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም ለ3 ወራት የሚያገለግል በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ጋራንቲ (ቢድ ቦንድ)
በጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች የሚገኙበት አድራሻ አማራ ክልል አዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
ግቢ ውስጥ ነው፡፡
8. በጨረታው ተሳትፎ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ከፋብሪካው ጋር ውል በመያዝ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ሙሉ
ክፍያ ቅድሚያ ከፍሎ ማንሳት የሚችል መሆን አለበት፡፡
9. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ