አዲስ ዘመን ዓርብ ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የተለያዩ ተቋማት የሆኑ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን እና በቁርጥራጭ መልክ የሚወገዱ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ
አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
1.ተጫራቾች ከአፍንጮ በር ወደ 6 ኪሎ በሚወስደው መንገድ ፍቅር ፕላዛ ህንፃ ላይ በሚገኘው በአዲስ አበባ
ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመምጣት የተለያዩ ተቋማት ያገለገሉ
ተሽከርካሪዎች እና በስክራፕ መልክ የሚወገዱ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር
400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ጨምሮ ተገኝተው መግዛት ይችላሉ፡፡
2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም በፊደል ያለ
ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ቢሮ
ቁጥር 402 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚከፈትበት ሰዓት ድረስ ተጫራቾች
ሰነዱን ማስገባት ይችላሉ ፡፡
3. ተጫራቾች በአሃዝና በፊደል እንዲሁም በነጠላና በጥቅል በሰጡት ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ አገልገሎቱ
ከፍተኛውን ዋጋ ወስዶ ያወዳድራል፡፡
4. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለጽ በመጫረቻ ሠነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች በአንድ መለያ ቁጥር(መደብ) ስር ያለውን ንብረት ብዛት በሙሉ መጫረት አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ድረስ በመሄድ ንብረቱን አይተው መጫረት ወይም ዋጋ መስጠት አለባቸው፡፡ነገር
ግን ንብረቱን ሳያዩ ቢጫረቱና ቅሬታ ቢቀርብ አገልግሎቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡
7. ለሚገዙት የተለያዩ ተቋማት ተሽከርካሪዎችና በቁርጥራጭ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች የጨረታ መነሻ
ዋጋውን 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት
ማስወገድ አገልግሎት ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
8. የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ
በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 504 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ መክፈቻ
ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
9. ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም፡፡
10. ተሸከርካሪዎች የነበረባቸው የቦሎ ዕዳ እና የስም ዝውውር ወጪ በአሸናፊ ተጫራቾች ይሸፈናል፡፡
11.አንድ ተጫራች አንድ ተሽከርካሪ እና ከአንድ የመ/ቤት ንብረቶች በላይ መግዛት ይችላል፡፡ ሆኖም አንድ
ተጫራች ለአንድ ተሽከርካሪ፤ ለአንድ መደብ ንብረት የተለያየ ዋጋ በመስጠት መወዳደር አይችልም፡፡
12. በመነሻ ዋጋና በታች የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
13. የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ ኮድ ወይም መለያ ቁጥር ስጽፍ ተሳስቻለሁ ወይም ሳልጽፍ ቀርቻለሁ የሚሉ
ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
14. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን መክፈል
ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለአገልግሎቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
15. ንብረቱን በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
16. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ከጨረታው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋ
ማሻሻል ወይም መለወጥ አይችልም፡፡
17. የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውም ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-557-8671 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አገልግሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::