አዲስ ዘመን ቅዳሜ ግንቦት 9 ቀን 2017ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 005/2017 ዓ/ም
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት
የሚውሉ 1ኛ.የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዢ 2ኛ. የሞተር ሳይክል ግዥ 3ኛ, የስቴሽነሪና የጽዳት እቃዎች ግዥ 4ኛ. የጄኔሬተር ግዥ
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
በዚህም መሰረት ተጫራቾች ፦
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር
የTIN NO. ያላቸው ፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚገልጽ ታክስ ክሊራንስ ያላቸው እና
Online የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በህጋዊ ባንክ በተረጋገጠ CPO ለእያንዳንዱ ግዥ በተናጠል ከዚህ በታች
ከተ.ቁ 1 እስከ 4 በተቀመጠው መሰረት ከሚያቀርቡት የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር በተናጠል ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል ፡፡
2.1. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዢ ብር 20,000
2.2. የሞተር ሳይክል ግዥ ብር 25,000
2.3. የስቴሽነሪና የጽዳት እቃዎች ግዥ ብር 10,000
2.4. የጄኔሬተር ግዥ ብር 30,000
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፈርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ
ያለባቸው ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ፡፡
4. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 2.1 እስከ 2.4 ለተቀመጡት ለእያንዳንዳቸው የግዥ አይነቶች ለየብቻ
በማድረግ የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ ቴክኒካል መረጃዎችን በአንድ ኢንቨሎፕ ፖስታ በማሸግ ማለትም 1 ኦርጅናል እና 2 ኮፒ
በመለያየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ
ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ማስገባት
ይጠበቅባቸዋል፡፡
5. ይህ ጨረታ አየር ላይ የሚቆየው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ
ቀናት ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን በ04፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት 05፡00 ሰዓት ላይ
ቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የስብሰባ አዳራሽ ላይ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል ፡፡
6. ተጫራቾች |ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም ፡፡
7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው
የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል፡፡
8. ይህ የጨረታ ዋጋ ለ45 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የግዥ ዓይነት የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ብቻ በመክፈል
ቡታጅራ ከተማ አስ/ፋ/ጽ/ቤት የግ/ንብ/አስተ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 07 ቀርበው መግዛት ይችላሉ ፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046-145-67-77 ወይም 046-115-06-07 ደውሱ መጠየቅ ይቻላል
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ቡታጅራ