አዲስ ዘመን ረቡዕ ጥር 14 ቀን 2017
የጨረታ ማስታወቂያ
የምሥራቅ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት በ2017 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የበሰለ ምግብ አቅርቦት
ከመጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ለ4 (አራት) ተከታታይ ወራት የሚቆይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ
አገልግሎት ለማግኘት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN
Number) ያላቸው እንዲሁም አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ የሥራ ልምድ ያላቸው ሆኖ ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች በፌዴራል ገንዘብ ቢሮ የአቅራቢዎች መዝገብ ዌብሳይት ላይ ተመዝግበው ያሉ እና በአሁኑ ወቅት
ዌብሳይቱ ላይ መገኘታቸውን የሚያመላክት ኮፒ ማስያዝ የሚችሉ ወይም በክልሎች ገንዘብ ቢሮ የአቅራቢዎች መዝገብ ላይ የተመዘገቡ ሆኖ
ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የምግብ ማቅረቢያ ሜኑ ሙሉ በሙሉ መረዳት ይኖርባቸዋል።
5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፀውን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ
ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
6. የሚቀርቡትን የበሰሉ የምግብ አይነቶች በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት አሟልቶ ካላቀረበና ማንኛውም ስህተት
ቢፈፀም ኃላፊነቱ የተጫራቹ የአቅራቢው/ ድርጅት ይሆናል። እንዲሁም የታራሚዎቹ ምግብ የሚዘጋጀው በማረሚያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ
በተዘጋጀው ኩሽና ውስጥ ሆኖ የምግብ፣ የተለያዩ ማጣፈጫዎች እና የማገዶ እንጨት እንዲሁም ምግብ ማብሰያ እቃዎችን፣ ማንኛውንም ለምግብ
ማብሰያ የሚያገለግሉ ቁሳቁስ ሙሉ በራሳቸው ትራንስፖርት ወጪ ማረሚያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ እንደሚኖርባቸው ማወቅ ይኖርባቸዋል፤ ማንኛውም
ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,808.00 (ሶስት መቶ አስራ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ስምንት ብር ብቻ)
CPO ማስያዝ ይኖርበታል። በጨረታው የተሸነፉት ተጫራቾችም ተሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ ለጨረታ ማስከበሪያ በዋስትና ያስያዙት
CPO ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
7. አሸናፊው ድርጅት ከማረሚያ ቤቱ ጋር ውል መፈራረም ይኖርበታል። በተጨማሪም ማረሚያ ቤቱ የሚሰጠውን
ደንብ እና መመሪያ አክብሮ መሥራት ግዴታ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡፡
8. አሸናፊው ድርጅት በውሉ መሰረት የበሰሉ ምግቦችን በቀን ለአንድ የህግ ታራሚ በተቀመጠው ሜኑ መሰረት
ሳያቀርብ ቢቀር ውል ሰጪው በመንግሥት የግዥ መመሪያ ቁጥር 02/2004 እና FA 1/2009 እንዲሁም አዋጅ ቁጥር
157/2002 መሠረት ህጋዊ እርምጃ መውሰድ የሚችል መሆኑን መረዳት ይኖርበታል።
9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የበሰሉ ምግቦች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 (ሀምሳ ብር) በመክፈል
የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በምስራቅ
ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት ፋይናንስና አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና 2 (ሁለት) ኮፒውን በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው
ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የድርጅቱን ማህተምም ማድረግ ይኖርባቸዋል።
11. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) የሥራ
ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ይሸጥ እና ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ መሸጥ ከጀመረበት ቀን ጀምሮ እስከ (16) አስራ ስድስተኛው
የሥራ ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት
ማለትም በአስራ ስድስተኛው (16) የሥራ ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም በጨረታው ለመካፈል የፈለጉ ማናቸውም ወኪሎቻቸው
እንዲሁም የህግ ታራሚ ኮሚቴዎች እና ኮሚቴዎች በተገኙበት ይከፈታል። ይህ አስራ ስድስተኛው (16) የሥራ ቀን አመት በአል ከሆነ፣
በካላንደር ዝግ ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይሆናል፡፡
12. ማንኛውም ተጫራች ከሚወዳደሩባቸው የምግብ እህል ውስጥ አንድ አንድ ኪሎ ግራም ደረጃውን የጠበቀ ጤፍ፣
የምስር ክክ፣ የአተር ክክ፣ የተፈጨ በርበሬ፣ የዳቦ ዱቄት፤ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
13. ማንኛውም ተጫራች ማረሚያ ቤቱ በሚገኝበት አዳማ ከተማ ውስጥ የእህል ማከማቻ መጋዘን (ስቶር) ያላቸው
ሆኖ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
14. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ዋጋ ለቁርስ፣ ለምሳ እና ለእራት ለአንድ የህግ ታራሚ ብር
40.60 (አርባ ብር ከ 60/100) በመወደዳር የበሰለ ምግብ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት። ለዚህም የማቅረብ አቅሙን የሚያረጋግጥ
ከፍተኛ የገንዘብ መጠን የያዘ የባንክ ስቴትመንት መረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
15. አሸናፊው ድርጅት ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ
10% ብር 1,559,040.00 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሺህ አርባ ብር ብቻ) የውል ማስከበሪያ CPO ማቅረብ
ይኖርበታል፡፡
16. ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ
ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ገንዘብ ለማረሚያ ቤት ገቢ ሆኖ በግዥ መመሪያ ቁጥር 02/2004 እና EA 1/2009 እንዲሁም አዋጅ
ቁጥር 157/2002 መሠረት ማረሚያ ቤቱ ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡፡
17. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማብራሪያ፣ ማስተካከያ፣ ሃሳብ እና ጥያቄ ካለው ጨረታው ከመከፈቱ
ከ5 ቀን በፊት ለማረሚያ ቤቱ ማቅረብ ያለበት መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል። እንዲሁም ማረሚያ ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የማስተካከያ
ወይም ማሻሻያ ሃሳብ ካለው ጨረታው ከመከፈቱ 5 ቀን በፊት ለተጫራቾች ማሳወቅ የሚችል መሆኑን መረዳት ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን
ቀርቶ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚቀርበው የማስተካከያ ሃሳብም ሆነ ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
18. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-አዳማ ከተማ ዳቤ ሶሎቄ ዶነጎሬ ወረዳ ኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት፤
ስልክ፡- 022-212-41-55 ወይም 09-12-31-76-70 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡
የምሥራቅ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት አስተዳደር