አዲስ ዘመን ረቡዕ ጥቅምት 12 ቀን 2018ዓ.ም
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሐራጅ ጨረታ ቁጥር ሐጅ/05/2018
በ ሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል መጋዘን የሚገኙ የተወረሱ ንብረቶች የሐራጅ ሽያጭ
በጅቡቲ የባህር ወደብ ላይ የቆይታ ጊዜያቸው ያለፈ እና ወደ ኢትዮጲያ የተላኩ ዕቃዎች ወደ ሀገር ውስጥ
ገብተው በአስመጪዎቻቸው ጥቅም ላይ የሚውሉበትን ወይም የሚወገዱበት አኳኋን ለመወሰን በወጣው መመሪያ ቁጥር 33/2005 ተራ ቁጥር
4.7 ላይ እንደተመለከተው በጅቡቲ የባህር ወደብ ላይ የቆይታ ጊዜቸው ያለፈ ዕቃዎች ከጅቡቲ ወደብ ተጓጉዘው በኢትዮጲያ የጉምሩክ
ክልል ወደሚገኙ ደረቅ ወደቦች ወይም ሌሎች አመቺ የማከማቻ ሥፍራዎች ከደረሱበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አስመጪዎች
በዕቃዎቹ ላይ ሊከፈል የሚገባውን ቀረጥና ታክስ፤የወደብ አገልግሎት ክፍያ እንዲሁም ዕቃውን ከጅቡቲ ወደብ ለማጓጓዝ እና በደረቅ
ወደቦች ወይም በሌሎች አመቺ የማከማቻ ሥፍራዎች እንዲቆዩ ለማድረግ የወጣውን ማንኛውንም ወጪ ከፍለው ዕቃዎችን እንዲረከቡ እንደሚያደርግ
ነገር ግን አስመጪዎች በተሰጣቸው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚፈለግባቸውን ክፍያ ከፍለው ዕቃውን ካላነሱ እንደተተወ ዕቃዎች ተቆጥረው
በሐራጅ የሽያጭ ዘዴ እንደሚሸጡ እና ሽያጩን ወይም የማስወገድሥራውን እንዲያከናውን ለድርጅታችን የኢትዮጲያ የባህር ትራንስፖርትና
ሎጀስቲከስ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይህ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ወቷል።
ከታች በሰንጠረዥ 1 በተለያዩ ኮንቴይነር ቁጥር ከተራ ቁጥር 1 እስከ 10 የተመላከቱት ንብረቶች በንብረቶቹ
ትይዩ በተናጠል እና በጥቅል በተቀመጠው የሐራጅ ጨረታ መነሻ ዋጋ መሰረት በማድረግ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ላቀረበ፤የዘመኑን ግብር
ለከፈለ፤በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ ማቅረብ እና የጨረታ ማስከበሪያ 20% CPO የገንዘብ መጠን በንብረቶቹ ትይዩ የተቀመጠውን
የገንዘብ መጠን በድርጅታችን ሥም በማሰራት ማቅረብ ለቻለ ተጫራች የቀረበ ነው፡፡ ተጫራች በጥቅሉ በተመላከቱት ንብረቶች ላይ መወዳደር
የሚችሉት በጥቅሉ እንዲሁም በተናጠል በተመላከቱት ንብረቶች ላይ መወዳደር የሚችሉት በተናጠል በተቀመጠው መሰረት ብቻ ነው፡፡ በተራ
ቁጥር 11 ላይ የተመለከተውን ተሸከርካሪ በተቀመጠው የሐራጅ ጨረታ መነሻ ዋጋ መሰረት በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ 20% CPO
የገንዘብ መጠን በድርጅታችን ሥም በማሰራት ማቅረብ ለቻለ ማንኛውም ተጫራች የቀረበ ሲሆን ምንም አይነት ንግድ ፍቃድ አይጠይቅም።
ሰንጠረዥ 1 በተለያዩ ኮንቴይነር ውስጥ የሚገኙ ዕቃዎች ዝርዝር
|
S.N
|
Cargo Description
|
Container Number & Size
|
የሐራጅ ጨረታ መነሻ ዋጋ
|
መቅረብ ያለበት የሐራጅ ጨረታ ማስከበሪያ CPO 20%
|
|
1
|
SPINNING CARD
|
CAIU7756584/40 GP
|
3,034,579.93
|
606,915.99
|
|
SPINNING CARD
|
MEDU8570506/40 GP
|
|
2
|
PRINTING MACHINIERY
|
MEDU7119817/40 GP
|
1,900,695.20
|
380,139.04
|
|
3
|
PACKING PLANT EQUIPMENT
|
TCLU6557835/40 GP
|
3,715,287.47
|
743,057.49
|
|
TEMU2548745/20 GP
|
|
TCLU7419044/20 GP
|
|
|
|
TCNU3314438/40 GP
|
|
4
|
WASTED PLASTIC MATERIAL
|
UACU5664226/40 GP
|
8,675,997.89
|
1,735,199.58
|
|
UACU5557892/40 GP
|
|
UACU5618365/40 GP
|
|
BSIU9592145/40 GP
|
|
UACU5439879/40 GP
|
|
TCNU8317949/40 GP
|
|
HLBU2256568/40 GP
|
|
FCIU7222355/40 GP
|
|
XINU8220002/40 GP
|
|
UACU5480281/40 GP
|
|
5
|
SMOLOK DEEP
|
TCLU8326100/40 GP
|
1,049,575.20
|
209,915.04
|
|
6
|
MACHINERY ደቃቅ መጠን ያላቸው ጠጠሮች
|
BMOU1104280/20 GP
|
419,002.67
|
83,800.53
|
|
APZU3908407/20 GP
|
|
7
|
STEEL BULDINGS MATERIALS
|
FSCU9048642/40 GP
|
7,313,523.52
|
1,462,704.70
|
|
HLXU6297813/40 GP
|
|
TCKU6569280/40 GP
|
|
GESU5848679/40 GP
|
|
8
|
GLASS JAR
|
BMAU-6759640/40 GP
|
2,648,599.32
|
529,719.86
|
|
TCNU-1304929/40 GP
|
|
9
|
ROTEBIL GAS CH.
|
FCIU6072116/20 GP
|
2,924,886.80
|
584,977.36
|
|
10
|
HOTEL FURNITURE
|
CAIU7608036
|
16,701,613.76
|
3,340,322.75
|
|
HOTEL FURNITURE
|
MEDU4679823
|
|
HOTEL FURNITURE
|
FCIU9369999
|
|
HOTEL FURNITURE
|
MSCU-9934490
|
|
11
|
BUS
|
|
4,500,000.00
|
900,000.00
|
ከላይ ከሰንጠረዥ 1 እስከ 11 የተቀመጡትን የተለያዩ ንብረቶችን ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት /
ግለሰብ ከዚህ በታች የተመለከቱትን አስገዳጅ መመዘኛ መስፈርቶች አሟልቶ በሐራጅ ሽያጩ ላይ የመጫረት መብት አለው።
1. የተለያየ ፍቃድ የሚያስፈልጋቸው ንብረቶችን በተመለከተ ተጫራች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን
ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የሚያቀርብ እንዲሁም በተራ
ቁጥር 4 ላይ ለተመለከተው WASTED PLASTIC MATERIAL የሚጫረት ማንኛውም ተጫራች ከፊደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ወይም ከክልል የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ በተጨማሪ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
2. በተራ ቁጥር 11 ላይ የተመለከተውን ባስ ተሸከርካሪ ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛም ድርጅት ወይም ግለሰብ
መጫረት የሚችል ሲሆን የተሽከርካሪው የሐራጅ ሽያጭ ንግድ ፍቃድ አይጠይቅም፡፡ ለተሽከርካሪው ህጋዊ ሰነድ ከሟሟላት ጋር ተያይዞ
ያሉ ማንኛውም ወጪዎች የጨረታው አሸናፊ የሆነው ገዥ ግለሰብ/ድርጅት የመክፈል ግዴታ አለበት።
3. ማንኛውም መመዘኛ መስፈርቱን ያሟላ ተጫራች ይህ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ
ቀን ከወጣበት ረቡዕ ጥቅምት 12 ቀን 2017ዓ.ም ጀምሮ ቅዳሜን፤ እሁድን እና ህዝባዊና ኃይማኖታዊ በአላትን ጨምሮ ባሉት 15
/ አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሐራጅ ጨረታ ሂደቱ መሳተፍ የሚችል ሲሆን የሐራጅ ጨረታው ረቡዕ ጥቅምት 26 ቀን 2018ዓ.ም
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ይካሄዳል።
4. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው የሐራጅ የጨረታ ሂደቱ ከተከናወነ በኋላ ውጤቱ ለድርጅቱ የበላይ አመራር
ቀርቦ ውሳኔ ከተሰጠ እንዲሁም የአሸናፊው ውጤት በድርጅቱ ማስታወቂያ ቦርድ ላይ ለ3 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከተለጠፈና ቅሬታም ካል
ቀርቦ ከተፈታ በኋላ ለአሸናፊው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ (Award Letter) እንዲደርሰው ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ይሆናል።
5. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሐራጅ ሽያጩ ላይ ከቀረቡ ተወዳዳሪዎች ውስጥ በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ይሆናል።
6. ከጨረታ መነሻ ዋጋ በታች ወይም እኩል መነሻ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።
7. በሐራጅ ጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ CPO የጨረታው ውጤት በድርጅቱ የማስታወቂያ
ቦርድ ላይ ለ3 ተከታታይ የሥራ ቀናት ተለጥፎ ከቆየ እና ቅሬታም ካልቀረበ ከተፈታ በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን አሸናፊ ለሆኑ
ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑበትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ከፍለው እንዳጠናቀቁ የሚመለስ ይሆናል።
8. በጨረታ ውጤቱ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ተጫራች የሐራጅ የጨረታ ውጤቱ በጊዜያዊነት ይፋ በሚደረግበት የሐራጅ
ሽያጭ ቦታ እና በእለቱ እንዲሁም ውጤቱ በድርጅቱ ማስታወቂያ ቦርድ ላይ ከተለጠፈበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 3 ሦስት/ ተከታታይ የሥራ
ቀናት ውስጥ ቅሬታውን በፅሁፍ ማቅረብ ይችላል።
9, በአንድ ዝርዝር ውስጥ ተካተው ወይም በነጠላ ለሐራጅ ሽያጭ ለቀረቡ ንብረቶች ጨረታ ከ3/ሦስት/ በታች
ተጫራች ማለትም ሁለት ተጫራች ብቻ ከቀረቡ እርስ በርስ እንዲጫረቱ እንዲሁም አንድ ተጫራች ብቻ ከቀረበ የሐራጅ ጨረታ መነሻ ዋጋ
ላይ 10% ጭማሬ ለማድረግ ከተስማማ እና ጉዳዩ ውሳኔ ለሚሰጥበት አካል ቀርቦ ከተወሰነ በውሳኔው መሰረት ሂደቱ የሚቀጥል ሲሆን
ካልተወሰነ ጨረታው ይሰረዛል።
10. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን
ዕቃ ዋጋ ድርጅቱ በሚያሳውቀው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የጨረታው አሸናፊ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ገንዘቡን
ገቢ ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ ወይም እቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
11. በሐራጅ የጨረታ ሂደት አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊ ለሆነበት ንብረት የሚጠበቅበትን ከፍያ ፈፅሞ
ሲቀርብ ከሻጭ ድርጅት ጋር የገዥና ሻጭ ውል የመዋዋል ግዴታ ያለበት ሲሆን ንብረቶቹንም በናሙና እይታ ወቅት ባየውና ተስማምቶ ዋጋ
ባቀረበውና አሽናፊ በሆነበት ሁኔታ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ የመረከብ ግዴታ አለበት።
12. አሸናፊው ግለሰብ ወይም ድርጅት ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ባደረገ በ15 /አስራ አምስት/ የስራ ቀናት
ውስጥ እቃውን መረከብ አለበት።
13. በጨረታው የተሸጠ እቃ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ካልተነሳ የመጋዘን ኪራይ አከፋፈል የሚተመነው በደረቅ
ወደብ አገልግሎት ታሪፍ መሰረት ሆኖ እቃው ከተሸጠበት ከ16ኛው ቀን ጀምሮ የገዛው ሰው እስከሚረከበው ድረስ የቆየበት ጊዜ ይሆናል።
14. ማንኛውም ተጫራች በጥቅል የቀረቡት ላይ መጫረት የሚችለው ጥቅል የተመለከቱትን ሁሉንም የዕቃ አይነቶች
አንድ ላይ ሲሆን ነጥሎ መወዳደር አይችልም።
15. ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ
በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO) በተቋሙ ትክክለኛ ስም (የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ) ሥም በማሠራት የሐራጅ ጨረታ
ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
16. በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ያላስያዙትን ተጫራቾች ድርጅቱ ከጨረታው ይሰርዛል።
17. የተለያዩ ንብረቶችን፤ ጀነሬተሮችን እና ተሽከርካሪን መመልከት የሚፈልጉ ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት
ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል መጋዘን በአካል በመሄድ ከታች በተመለከተው የጉብኝት ቀን እና ሰዓት ብቻ
መመልከት ይችላሉ።
18. የናሙና እይታ፣ የC.P.O ማስገቢያ እና የሐራጅ ሽያጭ መርሀ ግብር ከስር በተገለፀው መሰረት መሆኑን
እናሳውቃለን።
|
የዕቃው ዓይነት
|
የናሙና ዕይታ እና C.P. ማስገቢያ ቀንና ሰዓት
|
የሐራጅ ጨረታው የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት
|
|
የተለያዩ አይነት ንብረቶች፤ እና ተሽከርካሪ
|
-የናሙና ዕይታ ቀን፤
ሐሙስ ጥቅምት 13፤ ሰኞ ጥቅምት 17 ሐሙስ ጥቅምት 20፤ ሰኞ | ጥቅምት 24 ብቻ ነው፡፡
-የናሙና ዕይታ ሰዓት፤
ከጠዋት ከ3፡00 እስከ 6፡00 እና ከሰዓት 8፡00-11፡00 ሰዓት ብቻ CPO ማስገቢያ ቀንና ሰዓት፤
-ከአርብ ጥቅምት 14 ቀን
2018ዓ.ም ጀምሮ እስከ ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ባሉት የሥራ ቀናት እስክ ከሰዓት 11፡30 ድረስ
ብቻ
|
የሐራጅ ጨረታው የሚከናወንበት ቀን፤
ረቡዕ ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ጨረታው የሚጀመርበት ሰዓት ጠዋት ከ3፡00-6፡00
ሰዓት ከሰዓት ከ8፡00-12፡00 ሰዓት
|
ጥብቅ ማሳሰቢያ፡-
CPO እና ፍቃድ የሚፈለግባቸው ማስረጃዎች ማስገቢያ ከላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት ብቻ የድርጅቱ ዋና
መስሪያ ቤት በሚገኝበት ለገሀር 6ኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጨማሪ
መረጃ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0115549304/ 0115549478 መደወልና መረጃ ማግኘት ይቻላል።
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ