አዲስ ዘመን ማክሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2017ዓ.ም
በአብክመ የኦሮሞ ብዞን ገንዘብ መምሪያ በ 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለዞን ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት
የሚውሉ፤
1. የሠራተኞች የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ
2. የሠራተኞች የተዘጋጁ ልብሶች
3. የሠራተኞች ጫማ
4. ልዩ ልዩ የስፖርት ትጥቆች
5. የተሽከርካሪ ጎማዎችን
6. የተለያዩ የቱሪዝም መስህብ የሆኑ ቅርሶችን በተንቀሳቃሽ ካሜራ /ድሮን/ በዞኑ ውስጥ ባሉ ወረዳዎች
እና ቀበሌዎች በመንቀሳቀስ በፎቶ እና በቪዲዮ የማንሳትና መቅረፅ ሥራን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
1. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ አጠቃላይ የሚወዳደሩበት የግዢ መጠን
ከብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርና
የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾቾ ስሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ
1. በተራ ቁጥር 1 ላይ ለሚገኘው ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/
2. በተራ ቁጥር 2 ላይ ለሚገኘው ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር
3. በተራ ቁጥር 3 ላይ ለሚገኘው ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/
4. በተራ ቁጥር 4 ላይ ለሚገኘው ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/
5 በተራ ቁጥር 5 ላይ ለሚገኘው ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር
6. በተራ ቁጥር 6 ላይ ለሚገኘው ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/
በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይንም በገቢ መቀበያ ደረሰኝ በኦሮሞ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ ስም
በምርጫቸው በአንዱ ከዋና /original/ የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7.ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን
ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት 19/2/2017 ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን ማለትም 3/3/2017 ዓ.ም 1፡30 ሰዓት
ድረስ በኦሮሞ ብሄ/ዞን/ገንዘብ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 03 ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ብር 100 /አንድ መቶ
ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋናና ቅጂ /original and copy/ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ
ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ማለትም 04/03/2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኦሮሞ ዞን ገ/ኢ/ት/መምሪያ
ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ
4፡30 ሠዓት በግልጽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ዕለቱ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት
ይከፈታል፡፡
10. የጨረታ ውጤት ለአሸናፊ ድርጅቶች በአድራሻ ለተሸናፊዎች ደግሞ በግልባጭ በደብዳቤና በመምሪያው የውስጥ
ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል።
11.ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርቶ የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
12. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ - ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ መስመር 325 ኪ.ሜ ላይ ከሚሴ ከተማ እንገኛለን፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0335542119 ወይም 0335540364 ላይ በመደወል ማንኛውም መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን ገንዘብ ኢኮ/ት መምሪያ