አዲስ ዘመን አርብ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም
በድጋሚ የወጣ ብሔራዊ የጨረታ ማስታወቂያ
ፕሮጀክት፡- የጎንደር ስታድየም ዕድሳት- ክፍል 1
ቀጣሪ/ደንበኛ፡- የፋሲል ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
አድራሻ፡- ጎንደር፣ ኢትዮጵያ
1. የጨረታዎች ግብዣ ፡-
የፋሲል ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በመቀጠል የታተመባቸውን ጨረታዎች ልምድ ካላቸው ብቁ ዓለም አቀፍ አቅራቢዎችና ተጫራቾች የተከታዮቹ የስታድየም ቁሳቁሶች አቅርቦት፣ ዝርጋታ፣ ፍተሻ እና ትግበራ ይጋብዛሉ፡፡
እሽግ (ፓኬጅ) ሀ፣ የፊፋን ደረጃ የጠበቀ 60ሚሜ ስስ ሳር (ዋና/መጫ የካፍ ምድብ
3 ደረጃ አቅራቢዎች ብቻ በመቅረብና በመዘርጋት የፊፋ ፈቃድ ያላችው እንዲሁም እየተሰራበት ያለውን የፊፋን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ተቀባይነት ይኖራቸዋል ፡፡
እሽግ (ፓኬጅ) ለ፡ የተሟላ የውሃ መፋሰሻ (ኤችዲፒኢ የቧንቧ ምስመሮች፣ የውሃ
ማርከፍከፊያ፣ የፈሳሽ ባልቦላ፣ ፖምፖ፣ መቆጣጠሪ ሰሌዳዎች(ፓነሎች)፣ የቴሌቪዥን
መቀበያ፣ መለዋወጫዎች፣
እሽግ (ፓኬጅ) ሐ፡ የቡድን ተለዋጮችና የባለስልጣኖች መቀመጫዎች ከወንበር መጋረጃ ጋር፤
እሽግ (ፓኬጅ) መ፡ የግብ ቋሚዎች፣ መረቦች እና የማዕዘን ባንዲራዎች፤
2. ለተጫራቾች መመሪያዎች፡
- የጨረታ ገንዘብ፡ የኢትዮጵያ ብር(ኢት.ብር)፣
- የጨረታ ዋስትና ፡ 2% የጠቅላላው የጨረታ ዋጋ፣ በባንክ ዋስትና አግባብ፣
- የጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ፡ 90 ቀኖች ከማስረከቢያው ቀን ጀምሮ፣
- የማስረከቢያ ጊዜ፡ ተጫራቾች ሁሉንም መሳሪያዎች በ90 ቀኖች ውስጥ ያቀርባሉ፤ ያጓጉዛሉ፣ ያስገባሉ እንዲሁም ይተገብራሉ ፡፡
- የማቅረቢያ ቦታ፡ ጎንደር ከተማ ስታዲየም፣ ኢትዮጵያ፣
- ኢኮተርም፡ ኤፍኦቢ አዲስ አበባ፣ የመጨረሻ መዳረሻ ጎንደር ስታዲየም፣
3. አቅርቦትና የሥራዎች ደረጃ፡-
ስኬታማ ተጫራች
- ሁሉንም ማቴሪያሎች በተሟላ ሁኔታ ከስራ ዝርዝሮች ጋር ያቀርባል፡፡
- ስሱ የሹራብ ጨርቅ የፊፋ ዕውቅና ያለውና የፊፋን የጥራት ደረጃ ማረጋገጫ ከደጋፊ ሰነዶች ጋር ማቅረቡን ያረጋግጣል ፡፡
- በትንሹ ሶስት የፊፋ የተመሰከረላቸው የፒች መስመር ዝርጋታ በስኬት
መጠናቀቃቸውን ያሳያል ፡፡
- ሁሉንም ማቴሪያሎች ወደ ጎንደር ፕሮጀክት ሳይት ያጓጉዛል፡፡
- የተሟላ የመስመር ዝርጋታ፣ ፍተሻና የሁሉንም እሽጎን መሳካት ያረጋግጣል፡፡
- የፊፋን የመጨረሻ ፍተሻና የመስክ ሳር በሜዳ መኖር ከማስረከቡ በፊት ያረጋግጣል፡፡
- መተማመኛ፣ መለዋወጫዎችና የተሟላ ስልጠና ለአካባቢው የጥገና ሰራተኞች ይሰጣል፡፡
4. የደንበኛ ኃሳፊነቶች፡-
- ዕቃዎችን በቦታው ማራገፍ፣
- ለኤችዲፒኢ የቧንቧ መስመሮች ቦይ ቁፋሮና መልሶ ሙሌት፣
- የአየር ትኬት የአካባቢ መጓጓዣ ለመስመር ዘርጊ ቡድን መስጠት፣
- መጠለያ፣ ምሳ እና የውሎ አበል ለሁለት ሙያተኞች፣
- ነጠላ ፊዝ 240 ቦልት ኤሌክትሬክሲቲ በዝርጋታ ወቅት የመስጠት፣
5. የዋጋ ዝርዝር(ማጠቃለያ)፡-
እሽግ ሀ፡ ሲንቴቲክ ሳር
- የፊፋን ደረጃ የጠበቁ 60 ሚሜ ሰው ሰራሽ ሳር(አርንጓዴ ሎሚ መሠል፣ ነጭ መስመሮች አቅርቦ መትከል) 1,000 ሜ2 በሙጫ በመሸፈን በቴፒ ክር መስፋት
እሽግ ለ፡ የመስኑ ውሃ የማጠጣር ስርዓት
- ኤችቢፒኢ ቧንቧዎች 160 ሚሜ (30ሜ)፣ 90 ሚሜ (345 ሜ)
- ቫልቮች፣ የቫልብ ሳጥኖች፣ የአየር ግፊት ቀናሽ ቫልብ፣ አየር የሚለቁ ቫልቮች፣
- አውቶ ማቲክ ዲስክ ማጣሪያ፣ የአየር ግፊት ጌጆች፣ አየር የሚያስውጡ ባልቦች፣
- ዲኮደር ያለው መቆጣጠሪያ፣ ዲኮደሮች፣ ዲቢኣር ማገናኛዎች፣
- ፓምፕ ማስጀመሪያ መቀባበያ፣ ወፍራም ሽቦ፣ ኮንዲቶች፣
- ጉልበት ሰጭ ፓምፕ(46 ሜትር ኪዩብ/ በሰዓት ለእያንዳንዱ 85 ሜ አናት ) + መቆጣጠሪያ ሰሌዳ፣
- የውሃ ወለል ሙቀት/ ብርሃን መለኪያ(አንድ ፍሬ)፣
እሽግ ሐ፡ አግዳሚ ወንበሮች፡-
- የተጫዋቾች አግዳሚ ወንበሮች፡ 14 መቀመጫዎች × 2 አግዳሚ ወንበሮች፣
- የዳኞች አግዳሚ ወንበር 4 መቀመጫዎች ı አግዳሚ ወንበር፣
እሽግ መ፡ ግቦች እና መለዋወጫዎች፡-
- የእግር ኳስ እግር ቋሚዎች(7.32 ሜ × 2.44ሜ) የተዘነከ ብረት፣
- የግብ መረቦች( ጥንድ)፣
- የማዕዘን ባንዲራ ምሶሶዎች ከባንዲራዎች ጋር (8 ፍሬ)፣
6. ጊዜያት እና ሁኔታዎች፡-
- የክፍያ ጊዜያት፡ በተጫራቹ የሚወሰን ይሆናል (ለምሳሌ ቅድሚያ + መካከለኛ + የመጨረሻ ክፍያ የምስክር ወረቀት ሲሰጥ፣
- መተማመኛ ዋስትና በትንሹ 3 ዓመታት በሲንቴቲክ ሳር፣ 1 ዓመት በመስኖ ስርአትና መለዋወጫዎች፣
- ስልጠና፡ አቅራቢ ለአካባቢው ሰራተኞች በአሰራርና ጥገና ላይ በቦታው ስልጠና
ይሰጣል፣
የግምገማ መስፈርት፣
- ከስራ ዝርዝርና ከፊፋ መስፈርት ጋር አብሮ የሚሄድ ቴክኒካዊ ተስማሚነት፣
- በትንሹ ከተመሰከረላቸው የፊፋ አነስተኛ ፕሮጀክቶች የሶስት ፕሮጀክቶች የስራ
ልምድ፣
- ለሳሩ የፊፋን የተመሰከረለት ምስክረ ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የማቅረብና የመስመር ዝርጋታ የጊዜ ሰሌዳ፣
- የፋይናንስ ተወዳዳሪነት፣
የማስረከቢያ ዝርዝር ሁኔታዎች፡-
- የጨረታው መነሻ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ሆኖ ማቅረቢያው የመጨረሻ ቀን ህዳር 4 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ (በአካባቢ ሰዓት)፣
- ጨረታው የሚከፈት ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት የተጫራቾች ህጋዊ
ወኪሎች ባሉበት ነው፡፡
- የማስረከቢያ ቦታ፡ ፋሲል ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ፣ ጎንደር፣
ኢትዮጵያ፣
- ኤሌክትሮኒክ ማቅረብ አልተፈቀደም፡፡
8. ተፈላጊ የጨረታ አባሪዎች፡-
- የኩባንያው ማንነትና መገለጫዎች (በተመሳሳይ በፊፋ - የተመሰከረላቸው የፊፋ ፕሮጀክቶች)፣
- የቴክኒክ መረጃ ወረቀቶችና ማረጋገጫዎች (ፊፋን ጨምሮ ጥራት ያለው የፕሮጀክት ሳር)፣
- የሥራ ፕሮግራም (ማምረት፣ መላክ፣ መዘርጋት፣ ማረጋገጫ መስጠት)፣
- የተብራራ የዋጋ ዝርዝር (የዋጋ መጠን የኢትዮጵያ ብር)፣
- የታሰበ ክፍያ እና የዋስትና ጊዜ፣
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የታክስ ሰነዶች፣
9. የጨረታ ይዘት፡-
ተጫራቾች በሰም የታሸገ የጨረታ ሰነድ በሶስት የተለያዩ ኤንቬሎፖች ያቀርባሉ፣
1.ቴክኒካዊ ዕቅድ
- የኩባንያው ማንነትና ማጣቀሻዎች (ከፊፋ ተመሳሳይ - የተረጋገጠላቸው ፕሮጀክቶች)፣
- ቴክኒካዊ የመረጃ ወረቀቶችና ማረጋገጫዎች (የፊፋን ጥራት የጠበቀ ስለ ሳር፣ ስለመስኖ ስራና ክፍሎቹ)፣
- የሥራ ፕሮግራም (ማምረት፣ መላክ፣ መስመር ዝርጋታ፣ ማረጋገጫ መስጠት)፣
- የታሰበ ክፍያና ዋስትና፣ ጊዜያት፣
- ተቀባይነት ያላቸው የንግድና የታክስ ሰነዶች፣
2. የፋይናንስ ዕቅድ፡-
- የዋጋ ዝርዝር (በቀረበው የዋጋ ዝርዝር ሰነድ)፣
- ታሳቢ የክፍያ ጊዜያት፣
3. የጨረታ ዋስትና፡-
- 2% የጨረታ ዋጋ በባንክ የዋስትና ቅጽ መሠረት፣
10. ተጨማሪ የጨረታ መስፈርቶች ፡-
1. አጠቃላይ የስራ ልምድ፣
2. የፊፋን የተፈቀደ ሳር በማቅረብና በመትከል የተረጋገጠ የስራ ልምድ፣
3. አቅራቢው ጊዜ ያላለፈበትን የፊፋን የጥራት ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት፣
4. የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና እንዲሁም ቅድመ ሁኔታ የሌለበት የባንክ ዋስትና፣
ማሳሰቢያ፡- የፋሲል ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ማንኛውንም ወይም ሁሉንም ጨረታዎች በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
የፋሲል ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ስራ ኢንተርፕራይዝ