አዲስ ዘመን ሀሙስ ህዳር 12 ቀን 2017ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ BPM 0002/2017 ዓ/ም
በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በስሩ ላሉት ፖሊስ ጣቢዎች በ2017 በጀት
ዓመት ሎት 1 የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና የቧንቧ ዕቃዎች፣ ሎት 2. የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች እና ለፅዳት ሰራተኞች ልብስ እና
ቆዳ ጫማ፣ ሎት 3 የተለያዩ የፅህፈት ዕቃዎዎች፣ የፕሪንተር፣ የኮምፒውተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 4, የህትመት
ውጤቶች፣ ሎት 5. የመኪና ጎማ ግዥ፣ ሎት 6. የውሀ መያዣ ሮቶ፣ ሎት 7 የተለያዩ መድሃኒት እና የህከምና ዕቃዎች፣ ሎት 8.
ካዝና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን፡-
ስለዚህ፦ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ
የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውና የታደሰ የዘመኑ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
እንዲሁም ከአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ሎት ቁጥር የሎት ዝርዝር _________________ የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር
ሎት 1. የተለያያዩ የኤሌክትሪክ እና የቧንቧ ዕቃዎች………ብር 6,000.00 /ስድስት ሺህ ብር/
ሎት2. የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች እና ለፅዳት ሰራተኞች ልብስ እና ቆዳ ጫማ………….. ብር 3,000.00/ሶስት
ሺህ ብር/
ሎት 3. የተለያዩ የፅህፈት ዕቃዎች፣ የፕሪንተር፣ የኮምፒውተር እና የፎቶ ኮፒ ማሽን መለዋወጫ እቃዎች…..ብር
4,000.00 /አራት ሺህ ብር/
ሎት 4. የህትመት ወጤቶች…….ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/
ሎት 5. የመኪና ጎማ ግዥ………ብር 20,000.00 /ሀያ ሺህ ብር/
ሎት 6. ውሀ መያዣ ሮቶ……..ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/
ሎት 7. የተለያዩ መድሃኒት እና የህክምና ዕቃዎች……..ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/
ሎት 8. ካዝና…..ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/
ተጫራቾች በሎት 1፣ በሎት 2 እና በሎት 3 ላይ የፅህፈት ዕቃዎዎችን ብቻ ናሙና /ሳምፕል/ ጨረታ ከመከፈቱ
በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡ በሎት 3 የፕሪንተር ፣የኮምፒውተር እና የፎቶ ኮፒ ማሽን መለዋወጫ እቃዎች፣ በሎት 4፣ በሎት 5፣ በሎት
6፣ በሎት 7 እና በሎት 8 መስሪያ ቤቱ በሚያቀርበው ሳምፕል ወይም እስፔስፊኬሽን መሰረት ሲሆን በዚህ ጨረታ አማራጭ ዋጋ ማቅረብ
አይቻልም፡፡
5. ተጫራቾች ታክስን የሚከፍሉበት ከ/ከተማ የወረዳ ጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
::
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃዎች በእስፔስፊኬሽን መሰረት በጥራት ኮሚቴው ወይም በሙያተኛ ተረጋግጦ ገቢ
የሚደረግ ይሆናል፡፡
7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳቦችን መስሪያ ቤቱ በሰጣቸው የአንድ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ጠቅላላ
ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መሙላትና የድርጅታችሁን ማህተም፣ ፊርማ፣ ሙሉ ስም አድራሻቸውን እና ስልክ ቁጥር በመግለፅ አንድ ኦርጅናል
እና ኮፒውን በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው ::
8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀን የማይመለስ ብር 400.00
(አራት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
9. የጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን ንብረት በራሳቸው የትራንስፖርት ወጪ በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ
ንብረት ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ማንኛውም ተጫራቾች በፖስታ የታሸገ ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት
ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ በ2፡30 እሰከ 11፡30 ሰዓት በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወረዳ 14 አንበሳ ጋራጅ
ጀርባ ቦሌ ክ/ከተማ ገቢዎች አጠገብ ያለው ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 23 የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ለጨረታ በተዘጋጀው
ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚቻለው የጨረታ ሰነድ መሸጥ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ማስገባት የሚቻል
ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዛው ዕለት 4፡00 ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ ክ/ከተማ
ፖሊስ መምሪያ 2ተኛ ፎቅ ባዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የጨረታ መክፈቻ ቀን በስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ
ቀን ይከፈታል ፡፡
11. የቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፅ/ቤት የተሻለ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ
የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን /ፋይናንሻል/ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ
ማቅረብ አለባቸው፡፡
12. አሸናፊ ድርጅቶች የስራ ትዕዛዝ ከተሰጣቸው በ05 ቀን ውል በመፈፀም በተከታታይ 10 ቀን ውስጥ ስራውን
መጀመር አለባቸው፡፡ በተጨማሪም መ/ቤቱ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
ለበለጠ መረጃ 011-8-27-53-61 መደወል ይቻላል፡፡
በአዲስ አበባ አስተዳደር የቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ